የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የፓርቲዎች የምርጫ ምልክት መረጣ በመከናወን ላይ እንደሆነ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት እስከአሁን ድረስ 45 ያህል ፓርቲዎች ምልክቶቻቸውን እንዳስገቡ ቦርዱ አስታውቋል።
ይሁንና ቦርዱ ስድስት ፓርቲዎች ያስገቡት የምርጫ ምልክት ጥያቄ ያስነሳ በመሆኑ በቀጣይ ምላሽ እንደሚሰጥ ገልጿል።
ስድስቱ ፓርቲዎች የመረጧቸው ምልክቶች በተለያዩ ምክንያቶች ቀይረው እንዲያቀርቡ ጥሪ ከቀረበላቸው ፓርቲዎች መካከልም
1. የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ – የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ
2. የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ- የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ
3. የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ – የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ
4. የምእራብ ሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ – ከሌላ ፓርቲ ምልክት ጋር ምልክቱ የተቀራረበ በሆኑ
5. የአርጎባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያቂ ንቅናቄ- ከሌላ ፓርቲ ምልክት ጋር ምልክቱ የተቀራረበ በመሆኑ
በተጨማሪ
6. የኦሮሞ ነጻነት ግንባር – ህጋዊ ሃላፊነት በተሰጠው አካል ምልክታቸውን እንዲመርጡ የተጠየቁ (በዚህም መሰረት የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ የምርጫ ምልክት አስገብተዋል።)
በዚህ መሰረት የምርጫ ምልክቶቻችሁን ያላስገባችሁ፣ እንድትቀይሩ የተገለፀላችሁ ወይም መቀየር የምትፈልጉ እስከ ጥር 23 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንድታጠናቅቁ ቦርዱ እያሳሰበ የጸደቁ ምልክቶችን እና የፓርቲዎችን ዝርዝር ሂደቱ ሲጠናቀቅ ይፋ እንደሚያደርግ ቦርዱ አስታውቋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ጥር 18 ቀን 2013 ዓ.ም
