በመላው ትግራይ ኤሌክትሪክ ዳግም ተቋረጠ፡፡

የፅንፈኛው ህወሓት ርዝራዦች በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ በፈፀሙት ጥቃት በመላው ትግራይ ኤሌክትሪክ ዳግም ተቋርጧል፡፡

የፅንፈኛው ህወሓት ርዝራዦች አዲጉዶም በተባለ አካባቢ ከአላማጣ – መሆኒ – መቐለ በተዘረጋው ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ባደረሱት ጥቃት ነው በክልሉ ኤሌክትሪክ የተቋረጠው ብሏል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ፡፡

ከዚህ ቀደም መስመሩ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት እንደነበረና ለመጠገንም ረዘም ያለ ጊዜ እንደወሰደ ይታወሳል፡፡

ክልሉ ኃይል ከሚያገኝባቸው መስመሮች አንዱ የአላማጣ – መሆኒ – መቐለ መስመር ሲሆን የተከዜ አክሱም መስመር ደግሞ የጥገና ሥራው እየተከናወነ እንደነበር መገለፁ አይዘነጋም፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የወደመውን መሰረተ ልማት ዳግም በመጠገን መልሶ ኃይል ለመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ መረጃው ያመለክታል፡፡

የካቲት 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *