የ125ኛው የአድዋ ድል በዓል ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች በተገኙበት ሊከበር ነው።

በአዲስ አበባ በሚከበረው በዚህ 125ኛው የአድዋ በዓል ፕሮግራም ከአገሪቱ ሁሉም አካባቢዎች የተውጣጡ ሰዎች እንደሚሳተፉ የሰላም ሚንስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።

በነገው ዕለት በሚካሄደው በዓል ላይ ከሁሉም ዩንቨርሲቲዎች የተውጣጡ የታሪክ ምሁራን፣ የማህበረሰብ ተወካዮች፣ ዲፕሎማቶች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ፖለቲከኞች፣ የሀይማኖት መሪዎች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ይሳተፋሉ ተብሏል።

ከ50 ሺህ በላይ የሚሳተፉበት ይህ 125ኛው የአድዋ ድል በዓል በሸገር ፓርክ አልያም በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚካሄድ ኢትዮ ኤፍ ኤም ከአዘጋጆቹ ሰምቷል።

የአድዋ ድል ጣልያን በ1888 ዓ.ም ወይም ከ125 ዓመት በፊት ኢትዮጵያን ቅኝ ለመግዛት በሚል በሰሜን ኢትዮጵያ በኩል ያደረገውን ወረራ በዳግማዊ ሚኒሊክ የአስተዳድር ዘመን መላው ኢትዮጵያውያን በጋራ ጠላትን ያሸነፉበት ታሪካዊ የጥቁር ህዝቦች ድል ነው።

በሳሙኤል አባተ
የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *