የቅዱስ ዻውሎስ ሆስፒታል ከደም ባንክ ጋር በመተባበር በ3 ቀናት ብቻ 100 ከረጢት ደም መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

የቅዱስ ዻውሎስ ሆስፒታል ከደም ባንክ ጋር በመቀናጀት መጋቢት 30 /2013 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 2/2013 ዓ.ም ድረስ የደም ማሰባሰብ ስራ መስራቱን ገልጿል፡፡

በዚህም 100 ከረጢት ደም መሰብሰቡን የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ የኮሚውኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ነዋይ ፀጋዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል:፡፡

አቶ ነዋይ እንዳሉት ለሶስት ቀናት የተደረገው የደም መሰበሰብ መርሃግብር ከሌላው ጊዜ ሲነጻጸር ጥሩ የሚባል መነቃቃት የታየበት መሆኑን ጠቁመው ደም ለጋሾች እንደመጡ ሳይጉላሉ ማስተናገድ መቻሉንም አቶ ነዋይ ለጣቢያችን ታናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም “O” የደም አይነት አለን ብለው የመጡ በዛ ያሉ ሰዎች እንደነበሩ እና እነርሱም እንደተስተናገዱ ጠቁመዋል፡፡

በደም መለገስ ሂደቱ ላይ ወጣቶች ከፍተኛውን ድርሻ ሲይዙ፣ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣መምህራን እና የጤና ባለሙያዎች አንደተሳተፉበት ነግረውናል፡፡

የሚሰበሰበው ደም በወሊድ ምክንያት የደም መፍሰስ ለሚያጋጥማቸው እናቶች እንደሚውል የገለፁት አቶ ነዋይ፣በአዲስ አበባ ከሚሰበሰበው አብዛኛውን ቅዱስ ጳውሎስ እና ጥቁር አንበሳ ሆስቲታል እንደሚወስድ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም ከሶስት ወር በኃላ የደም ልገሳ መርሃግብር እንደሚደረግ ገልፀው ህብረተሰቡ አሁንም ደም በመለገስ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

በረድኤት ገበየሁ
ሚያዝያ 04 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *