የ1 ሺህ 442ኛው የረመዳን ፆም ነገ ይጀመራል፡፡

የ1ሺህ 442ኛው የረመዳን ፆም ነገ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ገልጿል።

ምክር ቤቱ ለፋብኮ እንዳስታወቀው ሕዝበ ሙስሊሙ በፆምና በጸሎት የሚያሳልፈው የረመዳን ወር ነገ የሚጀምረው ጨረቃ ዛሬ በመታየቷ ነው።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ኡመር ኢድሪስ ወሩን በመረዳዳት በመተሳሰብና ከምንም በላይ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ በመስጠት ሕዝበ ሙስሊሙ እንዲያሳልፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሚያዝያ 04 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *