በባምባሲ ወረዳ ከ 50 በመቶ በላይ መራጮች የምርጫ ካርድ መውሰዳቸው ተነገረ፡፡

ከ 50 በመቶ በላይ መራጮች የምርጫ ካርድ መዉሰዳቸዉን የወረዳው አስተዳደር አስታውቋል፡፡

ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን የባምባሲ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጃፋር መርቀኒ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት በወረዳዋ በሚገኙ 47 ቀበሌዎች ላይ የመራጮች ምዝገባውን ማካሄድ መቻሉን ነግረውናል፡፡

በዚህም ከ 50 በመቶ በላይ አፈፃፀም መመዝገብ ተችሏል ነው ያሉን ፡፡

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ዞን በምትገኘው ባምባሲ ወረዳ አምስት የፓለቲካ ፓርቲዎች የሚፎካከሩ ሲሆን መኢአድ፤ ኢዜማ፤ አብን፤ ቤቢን እና ብልፅግና ፓርቲዎች ለምርጫው እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡

በወረዳው የስጋት ቀጠና ናቸው ተብለው የተለዩ አካባቢዎችን በመለየትም የፀጥታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አስተዳደሩ ለጣቢያችን ነግረውናል፡፡

በወረዳው ከፀጥታ ጋር ተያይዞ ምንም የሚያሰጋ ነገር እንደሌለና ከአጎራባች ክልሎች ጋር አልፎ አልፎ ከሚፈጠር ችግር ውጪ በወረዳው ምንም አይነት የሚያሰጋ ነገር እንደሌለም ነዉ የገለጹት፡፡

በትናንትናው እለት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ የመራጮች ምዝገባን አስመልክተው የክልሎችን አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት በቤኒሻንጉል ጉምዝ 70 በመቶ መራጮች መመዝገባቸውን ገልፀዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በየዉልሰዉ ገዝሙ
ሚያዝያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *