ካማላ ሃሪስ ህገ-ወጥ ስደትን በማስመልከት ያደረጉት ንግግር ለከፍተኛ ትችት ዳርጓቸዋል፡፡

የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ካማላ ሀሪስ ህገወጥ ስደትን አስመልክቶ ለሜክሲኮ ማስጠንቀቂያ አዘል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ይህ ንግግራቸዉን ተከትሎ በመጀመሪያ ስደተኞች ያሉበትን ሁኔታ መመልከት ይቀድማል በሚል እየተተቹ ነዉ፡፡

ምክትል ፕሬዝዳንቷ ወደዚህ ድንበር በመሄድ ስደተኞቹን ተመልክተዋል ወይ በሚል ከጋዜጠኞቹ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ “እኔ ወደ አውሮፓ አልሄድኩም ፣ እየተጠቀሰ ወይንም እየተነሳው ያለው ጥያቄም አልገባኝም” የሚል ምላሽን ሰተዋል፡፡

ይህን ተከትሎ ነዉ ምክትል ፕሬዝዳንቷ ትችት እየቀረበባቸዉ የሚገኘዉ በዚህም የአሜሪካና ሜክሲኮ ድንበርን እንዲጎበኙ ጫና ውስጥ መግባቸው ተሰምቷል፡፡

የባይደን ቃል አቀባይ ጄን ፕሳኪ ካማላ ሃሪስን የአሜሪካ-ሜክሲኮን ድንበር ያልጎበኙት ለምን እንደሆነ ተጠይቀው ሲመልሱም “በተወሰነ ጊዜ ወደ ድንበሩ ሊሄዱ ይችላሉ ብዬ አስባለሁ” ሲሉ ምላሽ መስጠታቸውም ተሰምቷል፡፡

አሜሪካ የሜክሲኮ ሰራተኞችን መብት ለመደገፍ የሚያስችል 130 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ እንደምትለግስም ቃል ገብታለች ፡፡

እንዲሁም ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ እና በሃገሪቱ ለተከሰቱት አውሎ ንፋሶች ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ የሚውል 310 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለመለገስ ቃል መግባቷም ተሰምቷል ፡፡

በሜክሲኮ ድንበር ወደ ከ178 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰነድ አልባ ስደተኞች ይገኛሉ፤ይህ ደግሞ ከሃያ ዓመታት ወዲህ የታየ ከፍተኛው የስደተኞች ቁጥር በሚል ተመዝግቧል፡፡

ቢቢሲ

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በየዉልሰዉ ገዝሙ
ሰኔ 02 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *