የሴኔጋል ሆስፒታሎች በኮቪድ-19 ህመምተኞች ተጨናንቀዋል::

የሴኔጋል የጤና ሚኒስትር እንደገለፁት፣ በተለይም በመዲናዋ ዳካር የሚገኙ ሆስፒታሎች አቅማቸው ከሚፈቅደው በላይ በኮቪድ 19 ተጠቂዎች እየተጥለቀለቁ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ከባለፈው ወር ጀምሮ እየጨመረ የመጣው ተጠቂ ፤ አሁን በቀን እስከ 1 ሺህ 700 ደርሷል፡፡
አንድ ከፍተኛ የህብረተሰብ ጤና ሀላፊ እንደገለፁት ፤ በከተማዋ የህክምና ባለሙያዎችም እየተጠቁ ነው፣ 99 በመቶ የሆስፒታል አልጋዎችም ተይዘዋል ብለዋል፡፡

መመርመር የሚፈልጉ ሰዎች በመበርከታቸውም ላብራቶሪዎች ፤ በከፍተኛ ሁኔታ እየተቸገሩ መሆኑ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ጠበቅ ያለ ገደብ ሊጥሉ እንደሚችሉም የተገለጸ ሲሆን
ቀደም ሲል የሰአት እላፊና መሰብሰብ ላይ የተጣለው ገደብ ፤ መጋቢት ወር ላይ በተነሳዉ የተቃውሞ ሰልፍ መነሳቱ የሚታወስ ነው፡፡

ቢቢሲ

በሔኖክ አስራት

ሐምሌ 20 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *