ስደተኞችን ጭና ሚዲትራኒያንን ስታቋረጥ የነበረች መርከብ በመገልበጧ ቢያንስ 57 ሰዎች እንደሞቱ ተገለፀ


ከአቅሟ በላይ ስደተኞችን ጭና ከሊቢያ ወደብ የተነሳችው መርከብ በመገልበጧ ቢያንስ 57 ያህል ስደተኞች እንደሞቱ ተገልጧል፡፡

በሜዲትራኒያን በኩል አቋርጠው ወደ አውሮፓ ለመግባት የሚሞክሩ ስደተኞች ቁጥር ከምን ጊዜውም በላይ እንደጨመረ እየተገለፀ ነው፡፡

እንደ አለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም (IOM) ሪፖርት መሰረት ከሟቾች ውስጥ ሴቶችና ህፃናት ይገኙበታል፡፡

በወደቡ ጠባቂዎችና በአሳ አጥማጆች ረዳትነት ወደ ባህሩ ዳርቻ ህይወታቸው ተርፎ የመጡት ስደተኞች እንደገለፁት ከሆነ 20 ሴቶችና 2 ህፃናት ከሰመጡት ስደተኞች ውስጥ ናቸው፡፡

አውሮፓን ግብ አድርገው አደገኛውን የሚዲትራኒያን ባህር ለማቋረጥ የሞከሩ በርካታ ስደተኞች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

ከዚህኛው አደጋ በፊት 1500 ስደተኞች አውሮፓ ሳይደርሱ መሀል ላይ ወይም ሊቢያ ወደብ አካባቢ ጉዟቸው እደተጨናገፈባቸው የአለም አቀፉ ስደተኞች ተቋም (IOM) ገልጧል፡፡

ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ይሄ ወደ አውሮፓ የሚወስድ መስመር በስደተኞች ተጨናንቆ ነው የከረመው የአለም አቀፉ ስደተኞች ተቋም (IOM) መረጃ እንደሚያሳየው ፤ በዚህ አመት ብቻ ባህሩን አቋርጠው ወደ አውሮፓ ሊገቡ የሞከሩ 1200 ስደተኞች ሞተዋል፡፡

በ2020 በባህር አቋርጠው አውሮፓ ለመድረስ ሲሞክሩ ከሞቱ ስደተኞች የዘንድሮ ሟቾች ቁጥር በእጥፍ እንደሚበልጥ ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን ቻናላችንን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በሔኖክ አስራት
ሐምሌ 22 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *