ሶስት የኢትዮጵያ የቡና አይነቶች በአሊባባ ግሩፕ ተቀባይነት አገኙ፡፡

በቻይናዊው ጃ ክማ የሚመራው የአሊባባ ግሩፕ ለሶስት የኢትዮጵያ ቡናዎች እውቅና መስጠቱ ተሰምቷል፡፡

ዋይሊድ ፣ሃደሮ እና አራዳ የተሰኙ የቡና አይነቶች ናቸው በአሊባባ ግሩፕ አውቅና የተሰጣቸው፡፡

ዋይልድ ቡና ማኔጂንግ ዳሬክተር አቶ ገዛሃኝ ማሞ ለኢት ኤፍ ኤም እንደተናገሩት የአሊባባ ግሩፕ ባለቤት የሆኑት ጃክማ ወደ ኢትዮጵያ በመጡበት ጊዜ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ባደረጉት ውይይት አማካኝነት ቡናዎቹ ተቀባይነት አግኝተዋል ብለውናል፡፡

የንግድ እና የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ላለፉት አራት እና አምስት ወራት ያህል ቡናዎቹ በአሊባባ ግሩፕ ተቀባይነት እንዲያገኙ ከፍተኛ ጥረት ሲደርግ መቆየቱ አቶ ገዛሃኝ አክለው ተናግረዋል፡፡

አሁን በአሊባ ግሩፕ ስር የተካተቱት እነዚህ የቡና አይነቶች በተለያዩ የአውሮፓ እና የአፍሪካ ሀገራት በበይነ መረብ አማካኝነት ለሽያጭ ሲቀርቡ ነበር ብለዋል አቶ ገዛሃኝ፡፡

የኢትዮጵያ ስያሜ ያላቸው እነዚህ ቡናዎች በአሊባባ ድርጅት ውስጥ መካተታቸው ሀገሪቷ የውጭ ምንዛሬ በቀላሉ እንድታገኝ ያስችላታልም ብለዋል፡፡

ሶስቱ የቡና ምርቶች ከትላንትና ጀምሮ በአሊባበ ግፕ አማካኝነት ለሽያጭ መቅረባቸውን ነው ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ የተናገሩት፡፡

አሁን ላይ የኢትዮጵያ የቡና ምርቶች በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተቀባይነት እያገኙ እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ህዳር 24 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *