የህውሀት ቡድን አሁንም በአንዳንድ የአማራ አካባቢዎች እየተንቀሳቀሰ የህዝቡን ሰላም እየነሳ እንደሆነ ተገለፀ

የአማራ ክልል ኮምዩኒኬሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለጸው ህውሀት የሚባል አሸባሪ ቡድን እስካልከሰመ ድረስ ሰላም የሚባል ነገር አይታሰብም ብሏል፡፡

አሸባሪው የህውሀት ቡድን እስካልጠፋ ድረስ የክልሉ ብሎም የሀገር ሰላም አደጋ ላይ ይወድቃል ሲሉ የገለፁልን የክልሉ የኮምዩኒኬሽን ሀላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ናቸው፡፡

አቶ ግዛቸው ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት አሸባሪው የህውሀት ቡድን አሁንም በአንዳንድ የአማራ አካባቢዎች እየተንቀሳቀሰ የህዝቡን ሰላም እየነሳ ይገኛል ብለዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ በኮረም፣ በራያ፣ አደርቃይ እና በሌሎችም ቦታዎች እየተንቀሳቀሰ ዜጎችን እያፈናቀለ እና ዘረፋ እየፈጸመ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ይህ የሽብር ቡድን አቋሙን የሚቀይር ሀይል አይደለም በመሆኑም ቡድኑን ማክሰም ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የህውሀት የሽብር ቡድን እድል ካገኘ ያሰበውን ሁሉ ከማድረግ የሚቆጠብ ስላልሆነ በየትኛውም የክልሉ አካባቢዎች እድል ሊሰጠው አይገባም፤ ለዚህም ክልሉ ዝግጁ መሆኑን ነው ሀላፊው የተናገሩት፡፡

ነገር ግን ባለው ነባራዊ ሁኔታ አሁንም ሆነ ወደፊት ይህ ቡድን ለአማራ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያም ስጋት ነው ብለዋል አቶ ግዛቸው፡፡

ቡድኑ በሚንቀሳቀስባቸው ቦታዎች ሁሉ ዜጎችን ይገድላል ንብረት ያወድማል ተቋማት ላይ ዝርፊያ እና ውድመት ያደርሳል ይህ የቡድኑ መገለጫ ነው ብለዋል፡፡

አሁን እየተንቀሳቀሰባቸው ባሉ ቦታዎች እያደረገ ያለውም ይኸው ተግባሩ እንጂ አዲስ ባህሪ አይደለም እያንጸባረቀ የሚገኝው ያ ሲሆን የሽብር ቡድኑን ማክሰም ብቸኛው አማራጭ መንገድ ነው ሲሉ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 02 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *