ዩኒሴፍ ከ9 ሚሊዮን በላይ ህፃናት የፖሊዮ ክትባትን በዘመቻ ሊሰጥ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በደቡብ አፍሪካዊቷ ሀገር ማላዊ የፖሊዮ ወረርሽኝ መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ ፣ዩኒሴፍ በምስራቅና በደቡብ አፍሪካ ሀገራት የሚገኙ ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ ህፃናት በዘመቻው መልክ ክትባቱን ሊሰጥ እንደሆነ የድርጅቱ የምስራቅ እና የደቡብ አፍሪካ ቀጠናዊ ዳሬክተር ተናግረዋል፡፡

የቀጠናዊ ዳይሬክተር የሆኑት ሞሃመድ ኤም ፎል እንደተናገሩት ከሆነ “ይህ በአፍሪካ ውስጥ ከአምስት አመታት በላይ የተገኘ የዱር በሽታ የመጀመሪያው ምልክት ነው ” ያሉ ሲሆን ” ዩኒሴፍ ቫይረሱን ለመከላከል ከመንግስታት እና አጋር አካላት ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል ።

ፖሊዮን ለማስወገድ ያስችላል የተባለውን ዘመቻ ዩኒሴፍ የዓለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ ከሌሎችም አጋር ተቋማት ጋር በትላንትናው እለት በማላዊ ያስጀመረ ሲሆን ዘመቻ በሌሎች የቀጠናው ሀገራት እንደሚያስቀጥል አስታውቋል።

ሞዛምቢክ ፣ ታንዛኒያ እና ዛምቢያ ፣ ከማላዊ በመቀጠል የፊታችን ሃሙስ በዘመቻው አማካይነት ህፃናቶቻቸውን በመጀመሪያው ዙር ያስከትባሉ ተብሏል።

ግብረ ሰናይ ድርጅቱ በሁለት ዙሮች ተጠቃሚ ይሆናሉ ላላቸው 9 ሚሊዮን ህጻናት ከ36 ሚሊዮን በላይ የፖሊዮ ክትባት መግዛቱን ሲጂቲኤን ዘግቧዋል፡፡

ከእነዚህ ዙሮች በኋላ ከ20 ሚሊዮን የሚልቁ ህፃናትን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የክትባት ዘመቻዎች በቀጣይ ዙሮች እንደሚከናወኑ ዩኒሴፍ አስታውቋል፡፡

ረድኤት ገበየሁ
መጋቢት 12 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *