የፌደራል መሬት ባንክ እና ልማት ኮሚሽን ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልጉ ባለሃብቶች አዲስ እቅድ ማምጣቱን ገለፀ።

የፌደራል መሬት ባንክ እና ልማት ኮሚሽን ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልጉ ባለሃብቶች አዲስ እቅድ ማምጣቱን የኮሚሽኑ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሌንሳ መኮንን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

እርሳቸው እንዳሉት ለባለሃብቱ የታቀደው እቅድን በተመለከተ፣ ኮሚሽኑ ምን ያክል ይዞታ አለው፣ ለየትኛው ኢንቨቨስትመንት ይሆናል የሚለውን በቅድሚያ አጣርቷል ብለውናል፡፡

በተያያዘም ገበያ ወደ ኢትዮጲያ እንዴት እንሳብ የሚለውን ላይም እየሰራን እንገኛለን ነው ያሉት ፡፡

የታሰበው አዲስ እቅድ አለም አቀፋዊ የሆነ፣ በኢትዮጲያ ላይ የሚደረግ ከውጭ ኢንቨስትመንት ማድረግ የሚችሉ ኢነቨስተሮችን እንዲመጡ የሚጋብዝ መሆኑን ወ/ሮ ሌንሳ መኮንን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ኢንቨስት ለማድረግ ምቹ ሁኔታ የለም እየተባ የሚነሳውን ሃሳብ በተመለከተ ወና ዳይሬክተሯ ሲመልሱ ምቹ ሁኔታ እንኳ ባይኖር ይህ ሁኔታን ተቀብሎ ኢንቨስት ለማድግ ፈቅዶ የሚመጣን ለመቀበል እና ለማበረታታት እገዛም ለማድረግ ነው እየሰራን ያለነው ብለውናል፡፡

ለኢንቨስመንቱ ቅድሚያ የሚሰጠው በሚል የተለዩ ዘርፎችም የቤት ልማት ፣ ጤና እና የህክምና ተቋማት መገንባት ፣ ትምህርት ፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እንዲሁም ግብርና መሆናቸውን ተናግረዋል ፡፡

አቅምና ፈጠራን የሚያሳይ ፕሮፖዛል እንደሚቀበሉ የተናገሩ ሲሆን ፤ በፋይናንሱ ደግሞ ምን ያክል ያስወጣል የሚለውን ዝርዝር ፕሮፖዛል እንዲያመጡ እንጠብቃለንም ብለዋል።

በረድኤት ገበየሁ

ግንቦት 10 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *