የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ከሳዉዲ አረቢያ 2158 ዜጎችን ማስመለስ ተችሏል።
ተሰናባቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ከሳውዲ አረቢያ ዜጎችን የማስመለሱ ጥረት ይቀጥላል ብለዋል ።
በሳምንቱ ከሳውዲ ከተመለሱ ዜጎች በተጨማሪም ከታንዛኒያ 5መቶ ዜጎችን ማስመለስ እንደቸቻለ አምባሳደር ዲና አስታውቀዋል።
በቀጣይም በለያዩ ሀገራት በችግር ላይ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገራቸው ለማስመለስ ይሰራል ብለዋል ።
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከቃል አቀባይነታቸው ተነስተው የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር ጄነራል ሆነው መሾማቸው ይታወሳል ።
በምትካቸው በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ አለም ተሾመዋል።
በአባቱ መረቀ
ሰኔ 16 ቀን 2014 ዓ.ም











