የኢትዮጵያን የአየር ክልል ጥሶ ወደ ትግራይ ክልል ሊገባ የነበረ የጦር መሳሪያ የጫነ አዉሮፕላን መመታቱን የኢትዮጵያ መከላከያ አስታወቀ፡፡

በሱዳን አድርጎ የኢትዮጵያን አየር ክልል ጥሶ በሁመራ ሰሜናዊ ክፍል በኩል ወደ ትግራይ ሊያልፍ የነበረና ለሽብር ቡድኑ የጦር መሳሪያ ሊያቀበል የነበረ ማንንቱ ያልታወቀ አውፕላን በጀግናው አየር ሃይል ሌሊት አራት ሰዓት ላይ ተመትቶ መውደቁን መከላከያ አስታዉቋል፡፡

በሀገር መከላከያ ሠራዊት የመከላከያ ህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊ ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ እንደገለጹት፤የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስደፈር የሽብር ቡድኑን እየጋለቡ ያሉ ሃይሎች አሉ ብለዋል፡፡

ይሁን እንጅ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን ለማስክበር በተጠንቀቅ ላይ መሆናቸውን ሜጀር ጀነራሉ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም የሽብር ቡድን ሀገር የማፍረስ ህልሙን ትቶ ወደ ሰላማዊ መፍትሔ ካልመጣ እስከመጨረሻው ርምጃ ለመውሰዱ ሙሉ ዝግጅተ መደረጉን አስታዉቋል፡፡

ላለፉት በርካታ ወራት ከፍኛ ወታደራዊ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው አሸባሪው ህወሃት ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ኃይሉን ለውጊያ ሲያስጠጋ ነበር ተብሏል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *