ውዳሴ ዲያግኖስቲክስ ማዕከል ነጻ የጤና ምርመራ እና ህክምና አዘጋጅቻለሁ አለ፡፡

ማዕከሉ ጳጉሜን ከኛ ጋር በሚል መሪ ቃል ለ13ኛ ጊዜ 2ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች ነጻ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ምዝገባ መጀመሩን አስታዉቋል፡፡
ውዳሴ ዲያግኖስቲክስ ከጳጉሜ አንድ ቀን 2014 አመት ጀምሮ እስከ ቀጣዩ አመት ድረስ የሚቆይ የነጻ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጻል፡፡

የውዳሴ ዲያግኖስቲክስ ማዕከል ማኔጂንግ ዳሬክተር አቶ ዳዊት ሐይሉ እንደተናገሩት ከዚህ በፊት በነበሩት የበጎ አድራጎት ስራዎች ለ45ሺህ ያሀል ዜጎች ነጻ የህክምና አገልግሎት መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡
ነጻ የጤና ምርመራ አገልግሎቱን ማግኝት የሚፈልጉ ዜጎች ከጤና ባለሙያ የታዘዘላቸውን ምርመራ የሚገልጽ ወረቀት ይዘው ቢቻ በመምጣት አገልግሎቱን በየትኛውም ሰአት ማግኝት ይችላሉ ተብሏል፡፡

በማዕከሉ በሁሉም ቅርንጫፎች እንደ ኤክስሬይ አልትራሳውንድ እና ኤም አር አይ የመሳሰሉ አገልግሎቶች የሚሰጡ ይሆናል ሲሉ አቶ ዳዊት ተናግረዋል፡፡
ይህንን የነጻ የጤና ምርመራ ለማግኝት ዜጎች ወደ 9888 በመደወል መመዝገብ ይችላሉ ነው የተባለው፡፡

እንዲሁም ከዛሬ ነሀሴ 19/2014 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 5 ድረስ በስልክ ቁጥር
0943535353
0940050505
0940040404
ወይም 9888 በመደወል ከፍለው መታከም የማይችሉ ተመዝግበው በነጻ መታከም ይችላሉ ብሏል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *