ለወላጅ አልባ ህጻናት ድጋፍ የሚያደርግ “ውብ አንች” የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ፡፡

“ብሉ ብላንክ ሮዥ ፋዉንዴሽን” /BBRF/ ከአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ እና ከኢፌድሪ ሴቶች ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን ነው“ውብ አንች” የተሰኘውን ፕሮጀክት በዛሬው እለት ይፋ ያደረገው።

ፕሮጀክቱ ወላጅ አልባ የሆኑ ህጻናትን በማሰባሰብ፣የቤተሰብ ይዘት ያላቸው ቤቶችን በመገንባት ለመንከባከብ ዓላማ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡
ለዚህም ለቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት 200 ሚሊዮን ብር መመደቡን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

የአዲስ አበባ ሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሀና የሺጥላ “ቢ.ቢ.አር.ኤፍ /BBRF/ በተለያዩ ሁኔታዎች ከቢሯቸው ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልጸው፣ አሁን ደግሞ ወላጅ አልባ የሆኑ ህፃናትን በመሰብሰብ ለማሳደግ የጀመረው ስራ እንደ ከተማም ሆነ እንደ ሃገር ትልቅ ትውልድን የመታደግ ተግባር ነው ብለዋል፡፡

የኢፌድሪ ሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ማኒስቴር ሚነስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸዉ፣በአሁኑ ወቅት ድጋፍን የሚሹ በርካታ ህጻናት መኖራቸውን ጠቁመው የዚህ ፕሮጀክት ወደ ስራ መግባትም ሚናው በቀላሉ የሚታይ እንዳልሆነ አብራርተዋል፡፡

ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን በተለይም ህጻናትን መታደግ የሁላችንም ሃላፊነት ሊሆን ይገባል ያሉት ሚንስትሯ በዚሁ ዙሪያ ለሚሰሩ ተግባራት ሚንስቴር መስሪያ ቤታቸው ተባባሪ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

“ውብ አንች ፕሮጀክት” በአስገድዶ ደፋሪዎች ምክንያት በግፍ የተገደለችዉ “ዉብ አንች” ስም የተሰየመ ፕሮጀክት ሲሆን ‘ሁሉም ዕድል ለሁሉም ልጅ’ የሚል መሪ ቃል ይዞ ወደ ስራ መግባቱን የፕሮጀክቱ የሀገር ዉስጥ ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ፀደይ ተፈራ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በአቤል ደጀኔ
መጋቢት 14 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *