ቡና ባንክ የ11ኛ ዙር የውጭ ምንዛሬ ይቀበሉ፣ይመንዝሩ ፣ይሸለሙ መርሃ ግብር እድለኞችን ዛሬ ሸልሟል፡፡

መርሃ-ግብሩን በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ ያደረገው ቡና ባንክ፣ ደንበኞች የውጭ ሃገር ገንዘብን በባንኩ ሲመነዝሩ፣በተለያዩ ገንዘብ ማስተላለፊያ ድርጅቶች በኩል ገንዘብ ሲላክላቸውና በባንኩ በኩል ሲቀበሉ በእጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓቱ እድለኛ የሚሆኑ ደንበኞችን ተሸላሚ ያደርጋል።

ይህን ተግባሩ ላለፉት ስድስት ወራት ሲያደርግ እና እድለኞችን ሲሸልም መቆየቱን ባንኩ ገልጿል።

በተለይ ዛሬ ላይ ሃገራችን በጥቁር ገበያ እያጣች የምትገኘውን የውጭ ምንዛሬ ለመታደግ፣ ደንበኞች የውጭ ገንዘቦችን እንዲመነዝሩ ለማድረግ የማበረታቻ ሽልማቶች አስፈላጊ መሆናቸውን የባንኩ ማርኬቲንግ እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አባይነህ ሐብቴ ተናግረዋል።

አክለውም ሃገራት ለሚያከናውኗቸው የውጭ ሃገር ንግድ ልውውጥ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ከፍተኛ ችግር የሚፈጥር በመሆኑ፣ባንኮች ይህ እንዲቀር ለማድረግ ደንበኞች የውጭ ገንዘቦች በህጋዊ መንገድ እንዲያመነዝሩ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ዛሬ በተደረገው የእጣ አወጣጥ መርሃ-ግብር በአንደኛ እጣ የቤት አውቶሞቢል የመኪና ሽልማትን ጨምሮ፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽን ፣ዘመናዊ የውሃ ማጣሪያዎች እና ስማርት ስልኮች ለባለእደለኞች ወጥተዋል።

በዚህም መሰረት የአንደኛ እጣ የቤት አውቶሞቢል የመኪና ሽልማት የባንኩ የገርጂ ቅርንጫፍ ደንበኛ ወ/ሮ ጌጤ አማረ አሸናፊ መሆን ችለዋል።

የባንኩ የቤት አውቶሞቢል መኪና አሽናፊ በመሆን የወጣው የባንክ ቁጥር 0007510 ሆኗል።

በመሳይ ገ/መድህን
ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *