አሜሪካ፤ጃፓንና ፊሊፒንስ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ሊያካሂዱ ነዉ፡፡

የአሜሪካና የቻይና ዉጥረት እያየለ መምጣቱን ተከትሎ፣ ሁለቱ ሀገራት የወታደራዊ ዲፕሎማሲ እሽቅድምድም ዉስጥ ገብተዋል፡፡

አሜሪካ፤ ጃፓንና ፊሊፒንስ በደቡብ ቻይና የባህር ቀጠና ላይ የሚያደርጉት የባህር ኃይል ወታደራዊ ልምምድ በአይነቱ ልዩ ነዉ ተብሎለታል፡፡

ወታደራዊ ልምምዱ ከዛሬ ጀምሮ ለ 7 ቀናት እንደሚቆይም አልጄዚራ ዘግቧል፡፡

በዚህ የባህር ኃይል ወታደራዊ ልምምድ ላይ አዉስትራሊያም በተጋባዥነት ትሳተፋለች ተብሏል፡፡

ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ የቀጠናዉ ዉጥረት እየተባባሰ መምጣቱ ይነገራል፡፡

በታይዋን ጉዳይ የአሜሪካና የቻይና ዉዝግብ እየጠነከረ መምጣቱን ዘገባዉ አስታዉቋል፡፡

ዋሽንግተንና ቤጂንግ የቀጣናዉን የበላይነት ለመቆጣጠር በዉትድራና ዲፕሎማሲ ላይ መጠመዳቸዉም ተሰምቷል፡፡

በቅርቡ ቻይና ከሲናጋፖር፤ከካቦዲያና ሌኦስ ጋር ወታደራዊ ልምምድ ማካሄዷ የሚታወስ ነዉ፡፡

በአባቱ መረቀ
ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *