የከተማዋ ህዝበ ሙስሊም የዛሬውን ጁመዐ በሰላም እንዲያሳልፍ ጥሪ ቀርቧል።

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ የመስጅድ ፈረሳ ጋር በተያያዘ ማህበረሰቡ ያቀረበውን ህገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄዎች ማለትም የመስጅድ ፈረሳው ሙሉ በሙሉ እንዲቆም ፣የፈረሱትም መስጅዶች ወደ ቀድሞው ቦታቸው እንዲመለስ መሪ ድርጅቱ መጅሊስ ዘጠኝ አባላት ያሉት ኮሚቴ በማቋቋም በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት በተለያዩ ደረጃዎች ከሚገኙ የመንግስት አካላት ጋር እያደረገ ይገኛል ተብሏል ።

በመሆኑም መንግስትም የፍትህን መጓደል የጥያቄውን አሳሳቢነት፣በሸገር ሲቲ አስተዳደር በውይይት ላይ ያልተመሰረተን አካሄድን ከግንዛቤ በማስገባት ለተከሰተው የመብት ጥሰት ፍትህ የማስፈን ሚናውን በአፋጣኝ እንደሚወጣ ተስፋ እናደርጋለን ብሏል መግለጫው ።

በመሆኑም ኮሚቴው የደረሰበትን እስኪያሳውቀን ድረስ ውጤቱን በትእግስትና በዱአ እንዲጠባበቅ ለህዝበ ሙስሊሙ ጥሪ ቀርቧል።

የዛሬውን የጁመአ ሰላት የከተማዋ ሙስሊሞች በሁሉም መስጅዶች በሰላም ሰግዶ ወደ ቤቱ በሰላም እንዲመለስ መልእክት ተላልፏል።

በከተማዋ የሚገኙ ኢማሞች በሰላምና በትእግስት ዙሪያ የጁመአ ኹጥባ እንዲያደርጉም አሳስቧል።

ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.