በሀገሪቱ እያጋጠመ ያለዉ የሰዎች ስወራ እና የሀይል እርምጃ እንደሚያሳስባቸዉ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዋና ስራ አስፈፃሚዎች አስታዉቀዋል።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር መብራቱ አለሙ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለፁት ከሆነ በሀገሪቱ እየተፈጠረ ያለዉ የጋዜጠኞች እና የዜጎች ስወራ እንደሚያሳሰባቸዉ ገልፀዋል።

ሰብሳቢዉ የኢትዮጵያ ስብአዊ መብቶች እያወጣ ያለዉ ሪፖርት በጣም አሳሳቢ መሆኑን ገልፀዉ ይህ ህገወጥ ድርጊት በአፋጣኝ ሊቆም እንደሚገባ አስታዉቀዋል።

አቶ ፈይሰል አብዳላዚዝ የጋራ ምክር ቤት የዋና ስራ አስፈፃሚ አባል በበኩላቸዉ መንግስት የሀይል አካሄዶችን ሊያቆሞ ይገባል ብለዋል ከጣብያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ።

ቅድሚያ ለሚሰጣቸዉ ነገሮች በተለይም ለኑሮ ዉድነት፣ለሰላም እና ደህንነት እንዲሁም ለመልካም አስተዳደር ሁኔታ መንግስት ቅድሚያ ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

መንግስት ብቻዉን የሚያመጣዉ ለውጥ የለም ያሉት የዋና ስራ አስፈፃሚው አባል ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ከሲቪል ማህበራት እና ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ በመሆን ለዉይይት ዝግጁ መሆን አለበት ብለዋል።

በአቤል ደጀኔ

ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.