የካሳ ክፍያ በጊዜው ባለመከፈሉ የሚዛን አማን ኢንተርናሽል አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ማጓተቱን ተነገረ።

በ2013 አመት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የመሠረት ድንጋይ ተቀምጦለት ግንባታው የተጀመረው አየር ማረፈያው፣ ከካሳ አከፋፈል ጋር በተያያዘ የሚነሱ ቅሬታዎች በግንባታው ሂደት ላይ ችግር እየፈጠሩ ነው ተብሏል።

አየር ማረፈያው በሚገነባበት አካባቢ የሚገኙ የመሬት ባለንብረቶች ለመሬታቸው ማካካሻ የተተመነላቸው ካሳ በጊዜው እንዳልተከፈላቸው ተናግረዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተነገሩት፣ ፕሮጀክቱ የደረሰበትን ደረጃ በመለየት በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊሰሩ የሚችሉ ተግባራት ደረጃ በደረጃ እየተተገበሩ ናቸው።

አየር ማረፈያው ትልቅ ፕሮጀክት በመሆኑ ከፌደራል ጀምሮ በክልልና በዞን ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶት እየተገነባ መሆኑን ገልጸው፣ ክልሉ ለፕሮጀክቱ ቅድሚያ በመስጠት የበጀት ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል።

የሚዛን አማን አለም አቀፍ አየር ማረፈያ አጠቃላይ ግንባታው በሁለት አመት ተኩል ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ መገለጹ ይታወሳል።

@ፎቶ—-ፋይል
በሄኖክ ወ/ገብርኤል

ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *