በሻሸመኔ በቆሻሻ ውስጥ የተጣለ ቦምብ ፈንድቶ የ4 ልጆች ህይወት አለፈ

በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ ዛሬ ቆሻሻ ውስጥ ተጥሎ የነበረ ቦምብ ፈንድቶ ያገለገሉ ፕላስቲኮችን እየለቀሙ የሚተዳደሩ አራት ልጆች ህይወት አለፈ፡፡

ልጆቹ ያገለገሉ ፕላስቲኮችን እየለቀሙ ባለበት ሰዓት ከተጠራቀመ ቆሻሻ ውስጥ ቦምቡ መፈንዳቱ ተመላክቷል፡፡
በዚህም የአራት ልጆች ህይወታቸው ሲያልፍ፥ ሁለት ህፃናት ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

ህይወታቸው ካለፈ ልጆች ውስጥ ሶስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት መሆናቸውን በከተማው የሀሩፋ ክፍለ ከተማ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኢንስፔክተር ከማል ጄይላን መግለፃቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *