ዩክሬን 8 ሰፈሮችን ከሩሲያ ጦር ነፃ ማዉጣቷን አስታወቀች

ባለፈዉ ሳምንት ብዙ ሲነገርለት የነበረዉን መጠነ ሰፊ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ የጀመረዉ የፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ጦር በሩሲያ እጅ የገቡትን ትናንሽ ከተሞችን እያስመለሰ ነዉ ተብሏል፡፡

የዩክሬን ምክትል የመከላከያ ሚኒስትሯ ሃና ማሊያር ስምንት ከተሞቻችንን ከሩሲያ ጦር መንጋጋ ፈልቅቀን ወስደናል ማለታቸዉን ሲ ኤን ኤን አስነብቧል፡፡

እነዚህ ነጻ የወጡት የዩክሬን ከተሞች በዛፖርዢያና ባክህሙት አዉደ መሆናቸዉም ታዉቋል፡፡

የሩሲያዉ ፕሬዝዳንት ፑቲን ግን የዩክሬን የማሸነፍ እድል የጠበበ ብቻም ሳይሆን የተዘጋ ነዉ እያሉ ነዉ፡፡

ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *