በሱዳን እየተፋለሙ የሚገኙት ተፋላሚዎች የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡
የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከትናንት ጀምሮ ነው ተግባራዊ የተደረገው፡፡
የሱዳን ጦርና የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ተወካዮች፣ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ላለማድረግና በእግረኛ ሃይልም ሆነ የአየር ላይና የድሮን ጥቃት ላለመፈጸም ተስማምተዋል፡፡
ተፋላሚዎቹ ግጭት አቁመው የሰብአዊ ድጋፍ ለዜጎች እንዲደርስም ተባባሪ እንደሚሆኑ አረጋግጠዋል፡፡
ይሁን እንጂ ሁለት ወራት ባለፈው ጦርነት ሁለቱም ሃይሎች ለፈረሟቸው የተኩስ አቁም ስምምነቶች ተገዥ ባለመሆናቸው በዚህኛው ስምምነታቸው ላይ ጥርጣሬ እንዲፈጠር አድርጓል፡፡
ዋነኛ አደራዳሪዎቹ አሜሪካ እና ሳኡዲ ግን የተኩስ አቁም ስምምነቱ ተፈጻሚ የማይሆን ከሆነ የጂዳው ድርድር እንደሚቋረጥና ተከትሎ ሊመጣ የሚችለው እርምጃ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ እያስጠነቀቁ ነው።(አልጀዚራ)
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም
