ለሽረ ዕደስላሴ አዋሳኝ በሆኑት በሽራሮ እና ማይፀብሪ አካባቢዎች በኤርትራ ሰራዊት ተደጋጋሚ ትንኮሳ እየደረሰ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

የኤርትራ ሰራዊት ከሽራሮ 17 ኪሎ ሜትር ድረስ ተቆጣጥሮ በመያዝ በርካታ ግፎችን በትግራይ ህዝብ ላይ እየፈፀመ እንደሚገኝ ተገልፃል፡፡

የሽረ እዳስላሴ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ተፈሪ ሀይለመለኮት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣የኤርትራ ሰራዊት ከፍተኛ ትንኮሳ በየቀኑ እንደደሚፈፅማባቸው አስታውቀዋል፡፡

የኤርትራ ሰራዊት በባድመ፣ገምሀሎ እና በሽራሮ በኩል 17 ኪሎ ሜትር ድረስ በመዝለቅ ከብቶች የመዝረፍ፣ የመግደል እና ለእርሻ የተሰማሩ ሰዎች የመግድል እንቅስቃሴ አሁንም ተባብሶ እንደቀጠለ ገልፀውልናል፡፡

በማይፀበሪም በተለያዩ አከባቢዎች ከፍተኛ የሆነ ትንኮሳ እየደረሰበት እንደሚገኝ ምክትል ከንቲባው ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

ህብረተሰቡ በዚህ ድርጊት በከፍተኛ ሁኔታ የተማረረ መሆኑን የገለጹት ምክትል ከንቲባው፣ አሁንም ድረስ በሚድርስበት ጥቃት ክፉኛ እንደተጎዳ ተናግረዋል፡፡

የክልሉ መንግስት በሰላም ስምምነቱ ላይ ባለው አመኔታ ነገሮችን በትዕግስት እያለፈ እንደሚገኝም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ሰኔ 13 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *