የእስራኤል የፀጥታ ሃይሎች የጄኒን የስደተኞች ካምፕ ላይ ጥቃት ፈጽመው አምስት ፍልስጤማውያን ሲገድሉ በርካቶች ቆስለዋል።

ከተገደሉት ፍልስጤማውያን መካከል አንድ ህፃን ይገኝበታል።

የእስራኤል ጦር ወረራውን ያደረኩት ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ነው ሲል ገልጿል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሃላፊ፣ እስራኤል በፍልስጤም የምታካሂደውን ህገ-ወጥ ሰፈራ እንድታቆም አስጠንቅቀዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እስራኤል በፍልስጤም ግዛት ውስጥ የምታካሂደውን ኦፕሬሽ በአስቸኳይ እንድታቆም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት፣አምስት ፍልስጤማውያን ከተገደሉ በኋላ ሲሆን፣ ከሟቾች በተጨማሪ የእስራኤል ሃይሎች በሰነዘሩት ጥቃት ከ 90 በላይ ሰዎች ቆስለዋል መባሉን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በየውልሰው ገዝሙ
ሰኔ 13 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *