የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ ነበር የተባሉ ሶስት ፍልስጤማዊያን በእስራኤል ተገደሉ፡፡

በዌስት ባንክ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኝ በቱርሙስ አያ መንደር ውስጥ በመኪና ላይ ባነጣጠረ ጥቃት 3 ፍልስጤማውያን በእስራኤል የድሮን ጥቃት መገደላቸውን ፕሬስ ቲቪ ዘግቧል።

የእስራኤል ወታደሮች ጥቃቱን የፈፀሙት ግለሰቦቹ የሽብር ጥቃትን የሚፈጽሙ ቡድኖች አባል ከመሆናቸው ባሻገር የሽብር ድርጊት ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ ነበር ብለዋል፡፡

በዌስት ባንክ በዚህ ሳምንት ብቻ ከ12 በላይ ፍልስጤማውያን በእስራኤል ወታደሮች እንደተገደሉ መረጃው አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም በአካባቢው የሚኖሩ ከ200 በላይ የሚሆኑ የፍልስጤማዊያን የመኖሪያ ሕንፃዎች በእሳት መቃጠላቸው ነው የተገለጸው፡፡

በመሳይ ገ/መድህን

ሰኔ 15 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *