ኤሎን መስክ እና ማርክ ዙከርበርግ የቦክስ ግጥሚያ ሊያካሂዱ ነዉ፡፡

የዓለማችን ግዙፍ የኩባንያ ባለቤቶችና ስራ አስኪያጆች የሆኑት ሁለቱ ግለሰቦች የቦክስ ፍልሚያ ሊያካሂዱ መሆኑን ኢቭኒንግ ስታንዳርድ አስነብቧል፡፡

ይህ ድንገተኛ ሀሳብ የመጣዉ ሜታ ኩባንያ ትዊተርን የሚገዳደር አዲስ መተግበሪያ በስራ ላይ ማዋሉን ከለጠፈ በኋላ ነዉ፡፡

በዚህ ልጥፍ ስርም የትዊተር ባለቤቱ ኤለን መስክ ‹‹ ዙከርበርግ ከፈለገ እኔ ለቦክስ ግጥሚያ ዝግጁ ነኝ›› ሲል ይጽፋል፡፡

ይህን ሃሳብ የተቀበለ የሚመስለዉ የሜታ ኩባንያ ስራ አስኪያጅ ዙከርበርግ በኢንስታግራም ገጹ ላይ ኤለን መስክ የጻፈዉን ሃሳብ በፎቶ በማስደገፍ ‹‹ ቦታዉን አሳዉቀኝ›› ብሎታል፡፡

ኤለን መስክም በትዊተር ገጹ ‹‹ ቬጋስ ኦክታገን›› እንገናኝ ሲል የፍልሚያዉን ቦታ አስቀምጧል፡፡

መስክ በትዊተር ገጹ ላይ ‹‹ በተቀናቃኜ ሰዉነት ላይ ተኝቼ ተጋጣሚየን ምንም እንቅስቃሴ እንዳያደርግ የምገታበት ዘ ዋልረስ የሚባል ምት አለኝ›› ሲል አስፍሯል፡፡

ዙከርበርግ የጂትሱ ልምምድ በተደጋጋሚ እንደሚያደርግ በኢንስታግራም ገጹ ላይ የሚለጥፍ ሲሆን፣ ከ 6 ሳምንታት በፊትም የጂትሱ ዉድድር ማድረጉ እና የተለያዩ ሜዳሊያዎችን ማሸነፉን ተናግሮ ነበር፡፡

በወቅታዊ የፎርብስ መረጃ መሰረት ኤለን መስክ የ246 ቢሊዮን ዶላር ባለቤትና የዓለማችን ቀዳሚው ባለሃብት ሲሆን ዙከርበርግ ደግሞ በ100.9 ቢሊዮን ዶላር 11ኛው የዓለማችን ሃብታም ሰው ነው፡፡

በእስከዳር ግርማ
ሰኔ 15 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *