የተመድ ሰላም አስከባሪ ሃይል ከማሊ ለቆ እንዳይወጣ የሃገሪቱ አማጺ ሃይሎች አስታወቁ፡፡

ከአንድ ሳምንት በፊት የማሊ ወታደራዊ መንግስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ሀይል ከማሊ ለቆ እንዲወጣ ጠይቆ ነበር፡፡
ከዚህ በተቃረነ መልኩ የሃገሪቱ አማፂያን የሰላም አስከባሪ ሃይሉ በዛው በማሊ እንዲቆይ ጠይቀዋል፡፡

ሰላም አስካበሪ ሀይሉ ማሊን ለቅቆ የሚወጣ ከሆነ በሀገሪቱ ከፍተኛ ቀውስ እና ከፍተኛ አለመረጋጋት ይፈጠራል ሲል አማፂ ቡድኑ አሳስቧል፡፡

ይህው የአማፂ ቡድን በማሊ የተረጋገጠ እና አስተማማኝ ሰላም እስካልሰፈነ ድረስ የተመድ ሰላም አስከባሪ ሀይል ሀገሪቱን ለቆ መውጣቱ ችግሩ ዳግም እንዲያገረሽ ያደርገዋል ብሏል፡፡

የሰላም አስከባሪ ሀይሉ በማሊ ገብቶ ስራውን ከጀመረ አስር ዓመታት ቢቆጠሩም፣ ተጨባጭ መረጋጋት እና ሰላም እንዲፈጠር አላስቻለም የሚል ትችት ይቀርብበታል፡፡(አልጀዚራ)

በረድኤት ገበየሁ

ሰኔ 16 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.