ፒ.ኤስ.ጂ ኔይማርን ለአል ሂላል ለመሸጥ ተስማማ!

የሳኡዲ ፕሮ ሊግ ተወዳዳሪው አል ሂላል ለዝውውሩ 77.6 ሚ.ፓ ይከፍላል።

በሂደት የሚጨመር ክፍያ መኖሩም ተገልጿል።

የ31 ዓመቱ ተጫዋች ዝውውሩን ለማጠናቀቅ የህክምና ምርመራውን ማለፍ እና የወረቀት ስራዎችን ማጠናቀቅ ይኖርበታል።

ኔይማር በ2017 ባርሴሎናን ለቅቆ የፈረንሳዩን ክለብ የተቀላቀለው የዓለም የተጫዋቾች ዝውውር ክብረወሰን በሆነ 222 ሚ.ዩ እንደሆነ ይታወሳል።

ቅዳሜ ለት ፒኤስ ጂ የውድድር ዘመኑን የመጀመሪያ ጨዋታ ሲያከናውን የቡድኑ አካል አልነበረም።

የአሰልጣኝ ልዊስ ኤንሪኬ ዕቅድ አካል አለመሆኑም ታውቋል።

በአቤል ጀቤሳ

ነሃሴ 08 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *