ከ42 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ አስተማማኝነቱ ያልተረጋገጠ መድሀኒት እና የመድሀኒት ግብዓቶች ወደ ሀገር ዉስጥ እንዳይገቡ መደረጉን የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን አስታወቀ።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዛሬ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ከ26 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የመድሀኒት ምርቶች ፍቃድ አግኝተዉ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ሲደረግ፣ ከ42 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ መድሀኒቶች ደግሞ ፍቃድ መከልከላቸው ተገልጧል።

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አበራ ደነቀ የ2015 ዓ.ም አፈፃፀም ሪፖርታቸዉን ባቀረቡበት ወቅት ፣
33 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የህክምና መሳሪያዎች ወደ ሀገር ዉስጥ እንዳይገባ መደረጉንም አስታዉቀዋል።

ከምግብና ደህንነት ቁጥጥር ጋር በተያያዘ ምግብ መዝግቦ ፍቃድ መስጠት ላይ ከ2925 የምግብ ዓይነቶች መመዝገብ መቻሉን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

የምግብ ላብራቶሪ ጥራት ዉጤት የምግብ ዘይት፣ጁስ፣የጨቅላ ህፃናት የዱቄት ወተት የመሳሰሉትን 41 የምግብ ምሮቶችን ጨምሮ በአጠቃላይ 1392 የምግብ ናሙናዎች ወደ ሀገር ለመግባት ታቅዶ የነበረ ሲሆን፤ 1359 የምግብ ናሙናዎች መስፈርቱን ሲያሟሉ 26 በሂደት ላይ ያሉ 8 የሚሆኑት ደግሞ መስፈርት ባለሟሟላታቸዉ ወደ ሀገር እንዳይገቡ ተደሮጓል ተብሏል።

በመግለጫዉ የህዝብ ግኝኙነት ዳይሬክተሩ ከ1ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የንፅህና መጠበቂያዎች አስፈላጊውን ቁጥጥር በማድረግ መልቀቂያ ፍቃድ እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን፣ ከ75.5 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ተጭበርብሮ የተመረተ የመዋቢያ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ መደረጉንም በመግጫቸዉ አንስተዋል።

በ2015 ዓ.ም ቁጥጥር ከሚደረግባቸዉ ምርቶች ጋር በተያያዘ 4ዐ የሚሆኑ የወንጀል ክሶች አቤቱታ ማቅረቡን ያስታወቀው ባለስልጣኑ፣ 28 መዝገቦች በምርመራ ላይ ሲገኙ አንድ መዝገብ ውሳኔ መሰጠቱ በመግለጫ ላይ ተነስቷል፡፡

በአቤል ደጀኔ
ነሃሴ 09 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *