የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ሂውማን ራይትስ ዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች መገደላቸውን ገለፁ፡፡

ሂውማን ራይትስ ዎች ዛሬ ባስነበበው ሪፖርቱ ላይ፣ ከየመን ወደ ሳውዲ ድንበር አቋርጠው ለመግባት የሞከሩ ኢትዮጵያውያን ላይ በከባድ መሳሪያ ጭምር የታገዘ ግድያ እንደተፈፀመባቸው አስታውቋል፡፡

በዚህም በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎች በድንበር አቅራቢያ በተፈፀመባቸው ጥቃት ህይወታቸው እንዳለፈ ገልፃል፡፡

ሂውማን ራይትስ ዎች ቃል አቀባይ ለአጃንስ ፋራንስ ፕሬስ እንደገለፁት፣ 38 ስደተኛ እና አራት የቤተሰብ አባላት የሆኑ ኢትዮጵያውያንን ማናገሩን ገልጾ፣ ከመጋቢት 2022 እስከ ሰኔ 2023 ባለው ግዜ ውስጥ በሳወስዲ ድንበር ጠባቂዎች በከባድ መሳሪያ የታገዘ ተኩስ ሲከፈት እንዲሁም በርካቶች ሲሞቱ መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡

የሳውዲ ባለስለጣናት ከዚህ ቀደም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በድንበር ጠባቂዎች ስለሚደረግ ግድያ ተጠይቀው፣አስተባብለው የነበረ ሲሆን በአሁኑ ጥቃት ዙሪያ ግን ምንም ዓይነት አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

በአሁን ሰዓት በሳውዲ አረቢያ ከ750 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ሲኖሩ፣ከ450 ሺህ በላይ ወደ ሀገሪቱ በህገ-ወጥ መንገድ የገቡ መሆናቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ነሃሴ 15 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *