ተቋርጦ የነበረው የግእዝ ባንክ የአክሲዮን ሽያጭ ተጀመረ።

በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የግእዝ ባንክ የአክሲዮን ሽያጭ በድጋሚ ተጀምሯል።

በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት የአክሲዮን ሽያጭ እንቅስቃሴ በመቆሙ የባንኩን ምስረታ በተያዘለት ጊዜ ገደብ እንዳያከናውን ከፍተኛ መስተጓጎል ገጥሞት መቆየቱን አስታውቋል።

ግእዝ ባንክ አክሲዮን መሸጥ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በህብረተሰቡ ዘንድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተደራሽነቱን በማስፋት በወቅቱ የነበረውን የመመስረቻ ካፒታል ብር 500 ሚልየን ለማጠናቀቅ ከጫፍ ደርሶ እንደነበረም ገልጿል።

የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ የተፈጠረው መረጋጋት ከግምት ውስጥ በማስገባትና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅርበት በመነጋገር ተስተጓጉሎ የነበረውን የአክስዮን ሽያጭ እንደ አዲስ ማስጀመሩን አስታውቋል።

ባንኩ ባደረገው ከፍተኛ ጥረት በዚህ ወቅት ከ13ሺህ በላይ አክስዮን መሸጡን ገልጾ 1.8 ቢልዮን የተፈረመ ብር እና 850 ሚልዮን የተከፈለ ካፒታል መሸጡን ተናግሯል።

እንዲሁም በውጭ ሀገራት ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን አክስዮን ለመሸጥ በተከፈተው የውጭ ምንዛሬ የስዊፍት ኮድ 1.4 ሚሊየን ዶላር መሰብሰብ እንደቻለ ገልጿል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ነሃሴ 15 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *