ወጪ እንጂ ገቢ ባልጨመረበት ሆኔት በአስፈጻሚ አካላት የሚደረጉ የዋጋ መሻሻያዎች ሃገሪቱ ላይ ቀውስን እንጂ መፍትሄ ሊያመጡ አይችሉም ሲሉ የኢኮኖሚ ባለሞያ የሆኑት አቶ ስሜነህ ቤሴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
የዜጎች ገቢ ባልጨመረበት እና የዋጋ ግሽፈቱ 35 በመቶ በደረሰበት በዚህ ሆኔታ ላይ መንግስት በአገልግሎቶች ሆነ በምርቶች ላይ የዋጋ ማሻሻያ ማድረግ እንደማይገባው ገልጸዋል፡፡
በቅርቡ በታክሲ ትራንስፖርት ላይ መንግስት የዋጋ መሻሻያ ማድረጉን ያስታወሱት አቶ ስሜነህ ቤሴ በየጊዜው ምርት እና አገልግሎቶች ላይ የሚደረጉ የዋጋ መሻሻያዎች ምክኒያታዊነት እንደሚጎላቸው ገልጸዋል፡፡
ሲሆን ሲሆን መንግስት ማህበረሰቡን እየባሰ ከመጣው የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት ድጎማ ሊያደርግ ይገባው ነበረ ብለዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በአለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ በመጨመሩ የታክሲ አገልግሎት ለሚሰጡ የትራንስፖርት አይነቶች ይደረግ የነበረው የነዳጅ ድጎማ በመቆሙ ተደጋጋሚ የታክሲ የዋጋ መሻሻያዎች መደረጋቸው አይዘነጋም፡፡
በቅርቡም በተደረገው በታክሲ የዋጋ መሻሻያ ላይ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ለጣቢያችን የገለጹ ሲሆን መንግስት ይህንን ያደርገው ምንን መነሻ በማድረግ ነው ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
አክለውም በከባድ የኑሮ ፈተና ወስጥ ለሆነ ለከተማው ነዋሪ መስረታዊ ከሚባሉ ነገሮች አንዱ በሆነው ትራንስፖርት ላይ ዋጋ መጨመር ተገቢ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ የኢኮኖሚ ባለሞያው በትራንስፖርት ዋጋ ላይ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ምርቶች ላይ የሚደረጉ ጭማሪዎች ከጥናት ይልቅ ግምት ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
ስለሆነም ማንኛው ኢኮኖሚየዊ ውሳኔ እታች ያለውን ማህበረሰብ ጭምር ያካተተ ሊሆን እንደሚገባ የኢኮኖሚ ባለሞያ እና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ስሜነህ ቤሴ ገልጸዋል፡፡
ካልሆን ግን መሰል ውሳኔዎች መፍትሄን ከማምጣታቸው ይልቅ ሃገርን ወደ ሌላ ቀውስ እንደሚከቱ ተናግረዋል፡፡
መሳይ ገ/መድህን
ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም
