ከግራም በታች የዳቦ ምርቶችን ሲያቀርቡና ሲሸጡ የተገኙ ዳቦ ቤቶች ላይ እስከ ማሸግ የደረሰ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ተባለ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ከግራም በታች የሆነ የዳቦ ምርት ለሸማቾች ሲያቀርቡ የተገኙ 169 ዳቦ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ነው ያስታወቀው።

ባለፍት ሶስት ወራት ከ 70 ግራም በታች ዳቦ ለሸማቾች ሲያቀርቡ የተገኙ እና የዳቦ መሸጫ ዋጋ ያለጠፉ በከተማዋ የሚገኙ ዳቦ ቤቶች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሰውነት አየለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በከተማዋ 1 ሺህ 323 የግል ዳቦ ቤቶች መኖራቸውን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ 593 በሚሆኑት ላይ የክትትል እና ቁጥጥር ሂደት መከናወኑን ገልጸዋል።

169 የሚሆኑ ዳቦ ቤቶች ላይ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን፣ 83ቱ ከ70 ግራም በታች ዳቦ ለሸማች ሲያቀርቡ እና 86 የሚሆኑት የዳቦ መሸጫ ዋጋ ያለጠፉ ናቸው ብለዋል።

ከነዚህም ውስጥ 163 የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ሲታለፉ በ6 ዳቦ ቤቶች ላይ ደግሞ የማሸግ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ህዳር 03 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *