የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ለ 6 ወራት የሚሆን የኢንሱሊን መድሃኒት ማከማቸቱን አስታወቀ

ለሚቀጥሉት 6 ወራት ለስኳር ህመም የሚያስፈልገዉ የኢንሱሊን መድሃኒት ዕጥረት እንደማይኖር የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግሯል፡፡

አገልግሎቱ የህይወት አድን እና መሰረታዊ የሚባሉ መገልገያዎችን ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ አገራት እየገዛ ለህብረተሰቡ እያቀረበ እንደሚገኝ አስታውቋል።

አገልግሎቱ ለስኳር ህመም መድሃኒት የሆኑ 5 ዓይነት መድሃኒቶችንም እያቀረበ መሆኑን ገልጿል፡፡

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ የስኳር በሽታ መድሃኒት ለ6 ወራት በቂ ክምችት አለ ብለዋል፡፡

ዶ/ር አብዱልቃድር፣ የክምችት መጠኑ ከ6 ወራት በላይ እንዲሆን ለማድረግም 4 ዓይነት መድሀኒቶችን ከዉጭ እያስገባን ነዉ ሲሉ ተናግረዋል ።

ከዚህም ዉስጥ አንደኛውን አይነት መድሃኒት በዚህ ዓመት በአገር ዉስጥ ለማምረት ስራዎችን ጀምረናል ብለዋል፡፡

አገልግሎቱ ሶስት ዓይነት የኢንሱሊን መድሃኒቶችን እንደሚያቀርብ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፤ሶስቱም እንደአገር በቂ ክምችት እንዳላቸዉም ነዉ የገለጹት፡፡

ይሁን እንጅ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ለሚደርሱ ወረርሽኞች እንዲሁም ግጭቶች ቅድሚያ የሚያስፈልጉ ግብአቶች በመሆናቸው የህይወት አድን መድሃኒቶች እንደ ጓንት እና ስሪንጅ ያሉ የህክምና መገልገያዎች የፍላጎት መጠናቸዉ እየጨመረ እንደሚገኝም ተነግሯል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ህዳር 04 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *