ሞዴል እና ተዋናይት ምህረት ታደሰ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሆቴል ማርኬቲንግ ማህበር አምባሳደር ሆና ተሾመች፡፡

የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሆቴል ማርኬቲንግ ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታሁን አለሙ እንደተናገረችው፣ሞዴል እና ተዋናይት ምህረት ታደሰ የ2016 የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሆቴል ማርኬቲንግ ማህበር አምባሳደር ሆና መሾሟን ተናግረዋል።

ለቀጣይ አንድ አመትም በአምባሳደርነት እንደምታገለግል ተነግሯል፡፡

ሞዴል እና ተዋናይት ምህረት ታደሰ የተሰጣትን የአንባሳደርነት ሹመትን በተመለከተ እንደተናገረችው፣ በማህበሩ የተጣለባትን ሃላፊነት ለመወጣት፣ የሀገሪቷን ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ እና ባህላዊ የሆኑ ዋና ዋና የቱሪስት መስቦችን ለአለም የማስተዋወቅ ሃላፊነትን ለመወጣት የተቻላትን ሁሉ ጥረት እንደምታደርግ ተናገራለች።

እንዲሁም የቱሪዝም መዳረሻ የሚሆኑ አከባቢዎችንም ለአለም ለማሰተዋወቅ የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት ማቀዷንም ገልጻለች።

በተጨማሪም ማህበሩ ሃገሪቷ ያላትን የቱሪዝም መዳረሻ ይበልጥ ለማስተዋወቅ በተለያዩ ቋንቋዎች የሚተላለፍ የቴሌቪዥን ጣቢይ የመክፈት እቅድ እንዳለውም አስታውቋል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ህዳር 18 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *