በዞኑ ህዝብ መካከል ለረጅም ጊዜ ግጭቶችን ሲፈጥሩ የነበሩ ችግሮች በንግግር መፈታታቸውን ዞኑ ገለጸ፡፡

በአሪ ዞን በጂንካ ህዝብ መካከል ግጭቶችን ሲፈጥሩ የነበሩ ችግሮች፤አሁን ላይ በንግግር ተፈተው እርቅ መደረጉን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

ከዚህ በፊት በቀደመው ደቡብ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን አደረጃጀት ውስጥ 14 ብሄረሰቦች እንደነበሩ ተገልጿል፡፡

አሁን ላይ ግን በአዲሱ የክልል አደረጃጀት ዞኖቹ ለሁለት የተከፈሉ ሲሆን፣ የደቡብ ኦሞ ዞን እና የአሪ ዞን ተብለው መለየታቸው ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ ከዚህ በፊት በነበረው የደቡብ ኦሞ ዞን አደረጃጀት ውስጥ ባሉ ብሔረሰቦች መካከል ግጭቶችን ሲፈጥሩ የነበሩ በርካታ ችግሮች ነበሩ ተብሏል፡፡

በተለይ በ2014 ዓ.ም በርካታ ሰዎችን ለስደት የዳረገ እና በብዙ ሺህ ብር የሚቆጠሩ ንብረቶችን ያወደመ ግጭት መደረጉን የአሪ ዞን አስታውቋል፡፡

ነገር ግን አሁን ላይ ችግሮቹ በንግግር ተፈተው ፤በህዝቡ መካከል እርቅ መደረጉን የዞኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ የሱፍ አህመድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ በዞን አደረጃጀት ብንለያይም ፤ አንድ ህዝብ በመሆናችን፤ምንም አይነት ልዩነት በውስጣችን ሊኖር አይገባምም ብለዋል፡፡

ስለሆነም ያለፈውን በማረም ወደ ፊት በጋራ መስራት ያስፈልጋል ያሉት አቶ የሱፍ አህመድ፣ የተደረገው ንግግር እና እርቅ የዚህ አንዱ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን

ህዳር 18 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *