በትግራይ ክልል በኮሌራ ወረርሺኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ2መቶ በላይ ደርሷል፡፡

በክልሉ 10 ወረዳዎች ላይ በሽታዉ መከሰቱም ተገልጿል፡፡

የክልሉ መንግስት ቁጥጥር በማያደርግባቸዉ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ከ2መቶ በላይ ሰዎች በኮሌራ መያዛቸዉን ለማወቅ ችለናል፡፡

በእነዚህ ቦታዎች ላይ የተከሰተዉ የኮሌራ ወረርሺን በመላዉ ትግራይ አደጋ ሊሆን እንደሚችልም ስጋት መኖሩን በትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች አስተባባሪ የሆኑት አቶ መብርሃቶም ሀፍቱ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ቁጥጥር በማያደርግባቸዉ ቦታዎች ላይ በኮሌራ ወረርሺኝ ምክንያት የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉን የገለጹት አስተባባሪዉ፤ መረጃዉ ስለሌለን እንጂ በማህበረሰቡ ዉስጥ ከዚህ በላይ ሰዎች ህይወታቸዉ አልፏል ነዉ ያሉት፡፡

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ቁጥጥር በሚያደርግባቸዉ አከባቢዎች 26 ሰዎች መያዛቸዉን ገልጸዉ ከእነዚህ መሃከል ሶስቱ ህይወታቸዉ ማለፉንም ነግረዉናል፡፡

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሙሉለሙሉ በማይቆጣጠራቸዉ እንደ ኮረም እና አላማጣ ያሉ ወረዳዎች ላይ እያንዳንዳቸዉ ጋር ከ1መቶ በላይ ታካሚዎች መገኘታቸዉን ገልጸዉ፤በአላማጣ ሆስፒታል ሶስት ሰዎች ህይወታቸዉ ማለፉንም ነግረዉናል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ታህሳስ 11 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *