የእንሰት በሽታ የስልጤን ዞን ህዝብ ለድርቅ አደጋ ዳርጓል ተባለ

የስልጤ ዞን ነዋሪዎች ከፍተኛ የድርቅ ስጋት ውስጥ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡

በዞኑ በተከሰተ የእንሰት በሽታ ምክኒያት ከፍተኛ የሆነ የድርቅ ስጋት ውስጥ መግባታቸውን የስልጤ ዞን ነዋሪዎች ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

የእንሰት ተዋእጾ ምግቦች በአከባቢው እንደባህል ተደርጎ የሚወሰድባት የስልጤ ዞን በዚህ አመት በተከሰተ በሽታ በአከባቢው አብዛኛው ቦታ እንሰቶች እየወደሙ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

በዚህም ምክንያት በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ከምግብ እጥረት መከሰት ምክንያት የተነሳ ወደ አጎራባች ዞኖች እያመሩ እንደሚገኙ የዞኑ ነዋሪዎች ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ከምግብነት ባለፈ እንሰት የአብዛኛው የስልጤ ማህበረሰብ የገቢ ምንጩ ነው የሚሉት ነዋሪዎቹ ፤በሽታው የማህበረሰቡን ኢኮኖሚ ክፉኛ እየጎዳው እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

በሽታዉ አሁን ላይ በዞኑ በምእራብ እና ምስራቅ አዘርነስ ፤ እንዲሁም አሊቾ ወራዳዎች በስፋት ተከስቷል ተብሏል፡፡

የበሽታው መድሃኒትም ከምርምር ማዕከላት ተገኛቷል ቢባልም እንኳን ፤እስካሁን አርሶ አደሩ ጋር ደርሶ መፍትሔ ያመጣ ነገር የለም ሲሉ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

በየወረዳው በሚገኙ ነዋሪዎች የተነሱትን ቅሬታዎች በመያዝ ወደ የስልጤ ዞንን ጠይቀናል፡፡

እንደሚቀበላቸው፤የዞኑ ዋና አስተዳደር አቶ አሊ ከድር ችግሩ መከሰቱን ለጣቢያችን አረጋግጠዋል፡፡

በሽታውን ለመከላከል ጉዳዩ ከዞኑ አቅም በላይ በመሆኑ ፤የክልል እና የፌደራል መንግስት እገዛ እንዲያደርግ በተደጋጋሚ ቢጠየቅም ፤መጥቶ የተመለከተን አካል የለም ነው ያሉት፡፡

በጉዳዩ ላይ ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የወራቤ ዩንቨርሲቲ የምርምር እና የህትመት ዳይርክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር ከድር ኢብራሂም፤ በሽታው ለማጣራት ጥናት ላይ ነው የምንገኘው ብለዋል፡፡

ነገር ግን በዞኑ የሚገኘውን ችግር ለመቅረፍ የሚችሉ እቅዶቻችን ከበጀት እጥረት እና ከተለያዩ ነገሮች አንጻር የተገደቡ ናቸውም ብለዋል፡፡

በመሆኑም የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ ካስፈለገ የወራቤ ዩንቨርሲቲ ከፌደራል መንግስቱ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ተናግረዋል፡፡

ታህሳስ 11 ቀን 2016 ዓ.ም

መሳይ ገብረ መድህን

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *