በአማራ ክልል ባለዉ የፀጥታ ችግር ምክንያት 10 የደም ባንክ አገልግሎት ማዕከላት ደም መሰብሰብ አልቻሉም ተባለ ።

የኢትዮጲያ የደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታዬ በክልሉ ባለዉ የፀጥታ ችግር ምክንያት 10 የደም ባንክ አገልግሎት ማዕከላት ደም መሰብሰብ እንዳልቻሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታዉቀዋል ።

በዚህም እንደ ሀገር ለመሰብሰብ ከታቀደው የሩብ አመት አፈፃፀም 1 መቶ 68 ሺህ 7 መቶ ዩኒት የደም ከረጢት 1 መቶ 39 ሺ 5 መቶ 60 ከረጢት ደም 83 ከመቶ መፈፀሙን ገልፀዋል ።

የአምስት ቀን የቆይታ ጊዜ ያለውና ለካንሰር ታካሚዎች በብዛት የሚጠቀሙት የፕላት ሌት የደም አይነት በሚፈለገው መጠን ለታካሚዎች አገልግሎት ለመስጠት ችግር እንደ ፈጠረ ተናግረዋል ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ 47 የደም ባንክ አገልገሎት ሰጪ ተቋማት ቢኖሩም በሰሜኑ ክልል ባሉ የደም ባንክ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በተፈጠሩ አለመረጋጋት ምክንያት ደም ከማዕከል ሲላክ እንደ ነበረ ጠቅሰዋል።

የአለም የጤና ተቋም የአንድ ሀገር የደም አቅርቦት በቂ ሊሆን የሚችው 1 በመቶ የሚሆነው የሀገረቱ ማህበረሰብ ደም ሲለግስ እንደሆነ ያስቀምጣል፡፡

ህክምናውና ቴክኖሎጂ እያደገ በሄደ ቁጠር እንዲሁም የካንሰር ናየልብ የቀዶ ህክምና አገልገሎት እየሰፋ ሲመጣ እንደ ሀገር ከዛ በላይ እንዲኖር ያስገድዳል ።
ከፊታችን ያለውን የገና በዓል ስናከብር ደም ለተቸገሩ ወገኖቻችን ደም በመለገስ ህይወት እናትርፍ ሲሉ ጥሪ አቶ ሀብታሙ አቅረበዋል ።

በልዑል ወልዴ

ታህሳስ 23 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *