ከቀጣይ አመት ጀምሮ የ8ኛና የ12ኛ ክፍል የፈተና ምዝገባ የሚደረገው በዲጅታል መሆኑ ተገለፀ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከቀጣይ አመት ጀምሮ የፈተና ምዝገባ የማደርገው በዲጅታል ነው ብሏል።

አገልግሎቱ በዛሬው እለት ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ጋር በጋራ በሰጠው መግለጫ ነው ይሄን ያስታወቀው።

በየአመቱ በሃገር አቀፍ እና የክልል አቀፍ የፈተና ምዝገባዎች ሲደረጉ አገልግሎቱ በርካታ ሚሊየን ግብሮችን እንደሚያወጣ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ ተናግረዋል።

አሁን የፈተና አገልግሎቱ የፈተና ምዝግባዎችን በዲጅታል እንዲደረጉ የሚያደርግ በመሆኑ ይሄን ወጪ እንደሚያስቀር አንስተዋል።

ይህንንም ማሳካት እንዲቻል በተለያዩ የሃገሪቱ አከባቢዎች ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ለዚህም ከ32 ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞች ተመልምለው ወደ ተለያዩ አከባቢዎች ተደልድለዋል ብለዋል።

ተቋሙ የሚሰጠውን አገልግሎት በማዘመን በ2015 ዓ.ም የሙከራ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን አሁን ላይ በሙሉ ኃይል ወደ አገልግሎት መግባቱን ገልጿል።

በመሳይ ገብረ መድህን

ታህሳስ 24 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.