ከእስራኤል ጋር ጦርነት ዉስጥ የሚገኘዉ የፍልስጤሙ ሃማስ የሰሜን ኮሪያን የጦር መሳሪያ እንደታጠቀ ደቡብ ኮሪያ አስታዉቃለች፡፡
የደቡብ ኮሪያ የስለላ ተቋም ይፋ እንዳደረገዉ፤ ሃማስ በእስራኤል ጦርነት ሰሜን ኮሪያ ሰራሽ የጦር መሳሪያዎችን እየተጠቀመ ነዉ፡፡
የሃማስ ወታደሮቸ የሰሜን ኮሪያን ኤፍ 7 የተሰኙ ሮኬችን እንደታጠቁ ሴኡል ደርሼበታለሁ ብላለች፡፡
ይህ መሳሪያ ከሶቪየቱ አር ፒ ሂ 7 እና ከቻይናዉ ታይፕ 69-1 ተመሳሳይነት እንዳለዉም ሲ ኤን ኤን ዘግቧል፡፡
አባቱ መረቀ
ታህሳስ 30 ቀን 2016 ዓ.ም
