ግብጽ የእስራኤልን ጥያቄ ውድቅ አደረገች፡፡

እስራኤል ነጻ ቀጠና ለመቆጣጠር ለግብጽ ያቀረበችው ጥያቄ በግብጽ በኩል ውድቅ ተደርጓል፡፡

እስራኤል በጋዛ ያለውን ከጦርነት ነጻ ቀጣና ወይም በፈር ዞን ለመቆጣጠር ያቀረበችውን ጥያቄ ግብጽ ውድቅ ማድረጓን ሮይተርስ ነው የዘገበው።

ሮይተርስ ሶስት የጸጥታ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ግብጽ፣ እስራኤል በግብጽ-ጋዛ ድንበር መካከል ያለውን በፈር ዞን ለመቆጣጠር ያቀረበችውን ጥያቄ ግብጽ ውድቅ አድርጋዋለች።

ግብጽ ከጦርነት በኋላ ስለሚኖረው አስተዳደር ላይ ከማተኮር ይልቅ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ቅድሚያ ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ እየገለጸች ነው።

በእስራኤል የተከበበችው ጋዛ 13 ኪሎሜትር የሚረዝም ድንበር ከግብጽ ጋር ትጋራለች።

ግብጽ ከኳታር ጋር በመሆን በጋዛ ተኩስ አቁም እንዲደረግ እና ታጋቾች እንዲለቀቁ የመሪነት ሚና ተጫውታለች።

የግብጽ ምንጮች እንደገለጹት በእነዚህ ንግግሮች ወቅት እስራኤል ተጨማሪ ጥቃትን ለመከላከል በድንበር አካባቢ ያለውን ጠባብ የፊላደልፊ ኮሪዶር ለመቆጣጠር ጠይቃ ነበር።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *