በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው ‘ሞል ኢን አዲስ መተግበሪያ’ ሂደቶችን ለማመቻቸትና ምርታማነትን ለማሳደግ ይረዳል ተብሏል።
መተግበሪያው ተገልጋዮች ካሉበት ቦታ ሆነው በቀላሉ የሚፈልጉት ምርትና አገልግሎቶችን አድራሻ የሚጠቁም መሆኑ ተነግሯል።
የሚከራዩ ቢሮዎችን ፣የስራ ማስታወቂያዎችና የሌሎችንም መረጃዎች አድራሻ የሚያመላክት መተግበሪያ እንደሆነም ነው የተገለጸው።
እንዲሁም ባሉበት ቦታ ሆነው ማመልከት የሚችሉበት የህንፃ ባለቤቶች የሚያከራዩትን ቢሮ ያለምንም ደላላ ለማስተዋወቅ እንደሚረዳመወ ተገልጿል።
ከተመሰረት አምስት አመት የሆነው መልፋን ቴክ በቴክኖሎጂና በኢኖቬሽንና ዘርፍ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ሰምተናል።
ድርጅቱ ለ45 ሰዎች የስራ ዕድል መፍጠሩንና ከ14 በላይ መተግበሪያዎችን ማበልፀጉን አስታውቋል።
በአባቱ መረቀ
ጥር 07 ቀን 2016 ዓ.ም
