37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡበት መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

ጉባኤውን መጠናቀቅ አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ፥ በሶማሊያ መንግስት በኩል የቀረበው ውንጀላ ኢትዮጵያ ለእንግዶች ያደረገችውን እንክብካቤ የማይመጥን ነው ብለዋል።

ሁሉም መሪዎች ያለ ልዩነት አቀባበልና መስተንግዶ እንደተደረገላቸው ጠቁመው፥ ኢትዮጵያ እንደ አስተናጋጅ ሀገር ሙሉ ኃላፊነት ወስዳ መስራቷን ገልጸዋል።

የጦር መሳሪያ ይዞ ወደ ጉባኤው ለመግባት መሞከር፣ ትኩረት ለመሳብና ያልተገባ ወቀሳ ለመሰንዘር ባለመ መልኩ ክስ መቅረቡ አስገራሚ እንደነበረ አብራርተዋል።

ችግሩ በህብረቱ የጸጥታ አካላት ብስለት መፈታቱንም ተናግረዋል።

ጉባኤውን ለማስተናገድ ከተደረገው ቅድመ ዝግጅት ጀምሮ የተሳካ ስራ መሰራቱን የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታዋ፥ በጉባኤው ዋና ዋና ስኬቶችን ማንጸባረቅ ተችሏል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በጉባኤው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያ በትምህርት መስክ ያስመዘገበችውን ስኬት መግለጻቸውን አስታውሰዋል።

የቀዳማዊት እመቤቶች መድረክ ላይም ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ሴቶችን ያማከለ የትምህርት ስርዓት ለሀገር እድገት ያለውን ሚና በስፋት ማንጸባረቃቸውን አብራርተዋል።

ከበርካታ ሀገራትና ተቋማት ጋር የተደረጉ የሁለትዮሽ ውይይቶችም በጉባኤው የተገኘ ስኬት እንደነበረ በመግለጫው አንስተዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *