በሆስፒታሉ ታካሚዎችን በማጭበርበር ላይ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ በሆኑት ዶ/ር ሽመልስ ገዛኸኝ ለአንድ ሳምንት ያህል በተመራ የኦፕሬሽን ስራ በግቢው ውስጥ ከሃኪሞች ጋር እናገናኛለን፣ህክምናችሁን እናፋጥንላችኋለን በማለትና ተገልጋይ በመምሰል የማጭበርበር ስራቸውን ሲያከናውኑ ቆይተዋል፡፡

በዚህም በተደጋጋሚ ከአንድ ታካሚ 20ሺብር፣ከሌላ ታካሚ ደግሞ 15 ሺ ብር እንዲሁም ከተለያዩ ታካሚዎች ደግሞ የተለያዩ ሞባይሎችና የተለያዩ ቁሳቁሶችን በተለያዩ ጊዜያት ሲሰርቁ የነበሩ ሶስት ግለሰቦች በዛሬው እለት እጅ ከፈንጅ በመያዝ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

                                                                                                                            ይህ ኦፕሬሽን የተመራውና ክትትል የተደረገበት በሆስፒታሉ በተዘረጋው ዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጅ በሆነው ሲሲቲቪ ካሜራ ሲሆን የተያዙት ንብረቶችም በኤግዚቢትነት ተቀምጠዋል፡፡

                                                                                                                             የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሽመልስ ገዛኸኝ ሆስፒታሉ በቴክኖሎጅ የተደረገ ሲሲቲቪ ካሜራ ከተገጠመ በኋላ ድብቅ ተልዕኮ ያላቸው ዘራፊዎች እየተጋለጡ መሆናቸውን ጠቅሰው ለዚህም ተገልጋዩም ሆነ ሰራተኛው እራሳቸውን ከተመሳሳይ አጭበርባሪዎች በመጠበቅና ወንጀልን በጋራ መከላከል እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

@መረጃውን ያደረሰን ተክለማሪያም ሃይሉ ነው

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 19 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *