አንበሳ ከኢትዮጵያ ከቅርብ አመታት በኋላ ሊጠፋ ይችላል ተባለ

ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሰፊ ቁርኝት ያለው አንበሳ ከጊዜ በኋላ ቁጥሩ እየተመናመነ በመምጣቱ ምክንያት ከቅርብ አምታት በኋላ ሊጠፋ እንደሚችል በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የአንበሳ እና የስጋ በል እንስሳት ተመራማሪ የሆኑት አቶ ካህሳይ ገብረትንሳይ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ተመራማሪው ህገወጥ የነዋሪዎች ሰፈራ፣ የደን ጭፍጨፋ መኖር፣ የእርሻ ስራ እና ግጦሽ መበራከት አንበሶቹ የሚፈልጉትን ምግብ እንዳያገኙ ሆኗል ብለዋል።
በተጨማሪም በምግብ ሰንሰለት ውስጥ ችግር እንዲፈጠርና ለህገወጥ አደን በስፋት ተጋላጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ተብሏል።

በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የተለየ የአንበሳ ዝርያ ነው ተብሎ የሚታወቀው እና የመጥፋት አደጋ ያለበት የጥቁር ጎፈር አንበሳ ቢሆንም አሁን ላይ ግን በኢትዮጵያ ያሉ ሁሉም አንበሶች ላይ የመጥፋት አደጋ እንደተጋረጠባቸው ይገልጻሉ።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የባህል መድኃኒት ቀማሚዎች ፊታቸውን ወደ አንበሳ አጥንት ማዞራቸው እንስሳቶቹን ለህገወጥ አደን ይበልጥ ተጋላጭ እንዲሆኑና ቁጥራቸው እንዲመናመን ማድረጉን በ ተመራማሪው ይናገራሉ።

አቶ ካህሳይ ገብረትንሳይ ከኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጋር በባህልም ይሁን በሌላ ሰፊ ቁርኝት እንዳለው የሚነገረው አንበሳ ከመንገስትም ይሁን ከማህበረሰቡ ከፍተኛ ትኩረት ካልተደረገለት የአንበሳ ስሙ ብቻ ሊቀር እንደሚችል ስጋታቸውን ተናግረዋል።

አሁን ላይ ድሮ ከነበሩት አንበሶችን ቁጥር በግማሽ እንደቀነሰ የተናገሩት አቶ ካህሳይ የኢትዮጵያ አንበሶች ተገቢው ጥበቃ ካልተደረገላቸውም ሙሉ ለሙሉ የመጥፋት አደጋው ቅርብ ነው ሲሉ አሳስበዋል ፡፡

በለአለም አሰፋ

የካቲት 19 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *