ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፈው ወር ብቻ በወባ ምክንያት 764 ሰዎች መሞታቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ርዳታ ማስተባበሪያ /OCHA/ አስታወቀ።

እንደ ድርጅቱ ዘገባም በወባ ምክንያት በጥር ወር የ611 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን በየካቲት ወር በወባ የሞቱት ቁጥር በ25 በመቶ ከፍ ብሏል።

በወባ የታመሙ ሰዎች ቁጥር በዚህ ዓመት 5,2 ሚሊየን መድረሱን ያመለከተው OCHA በተለይም ኦሮሚያ፤ አማራ፤ ደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ ክልሎች የወባ ስርጭት ከፍ ማለቱ ተመልክቷል።

በቀዳሚነት ወባ ከተስፋፋባቸው ጋምቤላ ክልል እንዲሁም ደቡብ ምዕራብ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ዋነኛዎቹ ናቸው።

ምንም እንኳን ክትትል ለማድረግ እና የወባ ትንኞችንም ለመቆጣጠር የተባበረ ጥረት ቢደረግም በወባ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በተጠቀሱት ክልሎች መጨመሩን OCHA አስታውቋል።

ለወባ በሽታ መስፋፋትም መድኃኒት የተነከሩ የአልጋ አጎበሮችን አለመጠቀም፣ የመድኃኒት ርጭት በቂ አለመሆን፣ እንዲሁም ደካማ የሆነ የማኅበረሰብ የመከላከል ጥረት በዋና ምክንያትነት ተጠቅሷል።

የወባ በሽታን ስርጭት ለመቀነስ የወባ ትንኝ መራቢያ አካባቢዎችን ማድረቅና በመኝታ ጊዜም አጎበር መጠቀም በየጊዜው ይመከራል።

መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *